GebiWechi App

Take Control of Your Finance

የፋይናንስ እንቅስቃሴዎን በቀላሉ ይከታተሉ

ገቢ ወጪ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በቀን ተቀን እንቅስቃሴአቸው የሚያገኟቸውን ገቢዎችና ወጪዎች ለመቆጣጠር ያግዛቸዋል፡፡ በተጨማሪም ወጪዎቻቸውን ለተመረጠው የጊዜ ወሰን ገደብ ለቀን፣ ለሳምንት፣ ለወር ወይም ለአመት እንዲበጅቱ ይረዳቸዋል፡፡ ይህም ይሰራ ዘንድ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን መረጃዎች ለመተግበሪያው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህም መረጃዎች የገቢዎችና ወጪዎች የገንዘብ መጠን እና ለተመረጠው የጊዜ ወሰን ገደብ ላሉት ወጪዎች የታቀደውን የበጀት መጠን ናቸው፡፡

ገቢ ወጪ መተግበሪያ በግለሰብ ወይም በድርጅት የሚደረግን የገንዘብ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡ገቢ ወጪ መተግበሪያ ያስገቧቸውን መረጃዎች በማስላትና በማጠናቀር

ምን ያህል የገንዘብ መጠን ከተለያዩ የገቢ ምድቦች አይነት እንዳገኙ
ምን ያህል የገንዘብ መጠን ለተለያዩ የወጪ ምድቦች እንዳወጡ
. . . እና
ወጪዎችዎ በተመረጠው የበጀት ጊዜ ወሰን ገደብ ላይ ካለው በጀትዎ ጋር ምን ያህል መጣጣሙን

ለተመረጡት የጊዜ ወሰኖች የቀን፣ የሳምንት፣ የወር ወይም የዓመት ሪፖርቶችን ያዘጋጃል፡፡

Download Now